ታላቁ መጽሐፍ “ገንዘብን መውደድ የክፋት ኹሉ ሥር ነው፡፡” (1ኛ ጢሞ. 6፡
10) ሲል ወይም “ዐለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንደኾነ አታውቁምን?” (ያዕ. 4፣ 4) ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነው?
እግዚአብሔር ራሱ የፈጠረውን ዓለም መውደድ እንዴት ከእግዚአብሔር ጋር ሊያጣላ ይችላል? ደግሞስ ኦሪት ዘፍጥረት እግዚአብሔር
ፈጥሮ ሲጨርስ “ኹሉም መልካም እንደኾነ ዐየ” ይል የለምን? ታዲያ እንዴት መልካም ነገርን መውደድ መጥፎ ሊኾን ይችላል? ይህ
“ዐለምን መውደድ” የሚባለው መጥፎ ነገር ምን ማለት ነው?