Thursday, January 23, 2014

ምንባብና መልመጃ

ቀጥሎ ያቀረብኹላችኹ ትናንትና ሌሊት የአማርኛ አስተማሪዬ በሕልሜ መጥተው ያስተማሩኝን ነው፡፡ ከተመቻችኹ ሕልሜን ፍቱልኝ፡፡ “ካልተመቻችኹ በሊማሊሞ አቋርጡ” ያለው ማን ነበር? ሕልሙ እንዲኽ ነበር፡-

እንደምን አደራችኹ ተማሪዎች፡፡
ደኅና እግዚአብሔር ይመስገን መምህህህህህር፡፡
ቁጭ በሉ፡፡
እናመሰግናለን፡፡
አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ
ጐበናን ተሸዋ አሉላን ተትግሬ፣
ስመኝ አድሬያለኹ ትናንትና ዛሬ፣
ጐበናን ለጥይት አሉላን ለጭሬ፡፡
ተሰበሰቡና ተማማሉ ማላ፣
አሉላ ተትግሬ ጐበና (ከሸዋ)፣
ጎበና ሴት ልጁን ሊያስተምር ፈረስ፣
አሉላ ሴት ልጁን ጥይት ሊያስተኩስ፣
አገሬ ተባብራ ታልረገጠች እርካብ፣
ነገራችን ኹሉ የእንቧይ ካብ፣ የእንቧይ ካብ፡፡

ልጆች፣ እነዚኽን ስንኞች ከዚኽ በፊት የኾነ ቦታ ሲነገሩ ሰምታችኹ ይኾናል፡፡ አፍላቂያቸውን ስንቶቻችኹ እንደምታስታውሱ ግን እርግጠኛ አይደለኹም፡፡ አብሽር! ረኪና ሂንጅሩ! (ችግርየለም!) እኔ እነግራችኋለኹ፡፡ የእነዚኽ ውብ ስንኞች መፍለቂያቸው ዮፍታሔ ንጉሤ ይባላል፤ በሀገራችን የቴአትር ጥበባት ነገር ሲነሣ ስማቸው በግንባር ቀደም ከሚጠራላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይኽ ሰው ጎጃም ደብረ ኤልያስ ከቄሰ ገበዝ ንጉሤ ተወልዶ፣ ንባብ ቆጥሮ፣ ዜማ ቀጽሎ፣ ቅኔ ተቀኝቷል፡፡ ገና በ19 ዓመቱ ገደማም “ቀኝ ጌታ” ተብሏል፡፡ ከአባቱ ሞት በኋላ በገጠመው ማኅበራዊ ምስቅልቅል ወደ አዲስ አበባ ተሰድዶ መጣና እዚኽ ቀበና አቦ በድብትርና አገልግሏል፡፡ ቀጥሎም በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት በአማርኛ መምህርነት ተቀጥሮ ይሠራ ነበር፡፡ ኋላም የቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ዲሬክተር ኾኖ ሠርቷል፡፡ የምናብ እግሮቹ ወደ ቴአትሩ ዓለም ያመሩትም በዚኽ የመምህርነት ጊዜው ነው፡፡ ዮፍታሔ በ1920 ዓ.ም. ገደማ የጀመረው የድርሰት ሥራ የአምስት ዓመቱ የፋሽት ወረራ እስኪመጣ ድረስ ይበልጥ እያበበና እየፈካ ኼዶ እንደነበር የሕይወት ታሪኩን ያሰናዳው ዮሐንስ አድማሱ ይገልጣል፡፡ ዮፍታሔ የሀገር ፍቅር በእጅጉ ይሰማው የነበረ ሰው እንደኾነ ቴአትሮቹ ውስጥ ይስተዋል ነበር፡፡ ከላይ በመግቢያነት የሰፈረችው ቅንጭብም ይኽንኑ የሀገር ፍቅሩን ሳትጠቁም አትቀርም የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ ይኽንኑ ለማጽናት አንድ ሌላ ቅንጭብ ብጨምርላችኹ አይከፋኝም፡፡ ፋሽስት ቀስ እያለ ኢትዮጵያን ቅኝ የመግዛት ዓላማውን ሊያሳካ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ላይ ሲያደባ አካኼዱን የታሰበው ዮፍታሔ (1928) እንዲኽ ብሎ ነበር፡-

ከአገር ዕድሜ ተርፎ የሚቀረው ዕድሜ፣
ሞተ-ነፍስ ይባላል ልናገር ደግሜ፡፡
የፈሰሰ ስንዴ ተርፎ ከስልቻ፣
ለጌታው አይደለም ለዐይጥ መጫወቻ፡፡
ወታደር ገበሬ መጠንቀቅኽ የታል፣
ፍልፈልም ይገፋል፤ ዐፈር ይጎልታል፡፡

Thursday, January 16, 2014

ኦኔሲሞስ ነሚቺ ጉዳ!



በ1861 ዓ.ም. ገደማ በምዕራብ ሸዋ ሑሩሙ በምትባለው ስፍራ ባርያ ነጋዴዎች አንድ “ሒቃ አዋጂ” (ሒቃ ማለት በኦሮምኛ ተርጓሚ ማለት ነው፡፡) የሚባል የ14 ዓመት ታዳጊ ጠልፈው ወደ ምፅዋ ወሰዱት፡፡ ስምንት ጌቶችም በየተራ ተቀባበሉት፡፡ ገና በአራት ዐመቱ አባቱን ያጣ ልጅ እንዲኽ ያለ የመከራ ጽዋ ሲደመርበት ምን ያኽል ሕይወት መራር እንደምትኾንበት የደረሰበት ያውቀዋል፡፡
ምፅዋ ሲደርስ (ደግ ሰው አይጥፋ!) የስዊድን ሚሲዮናውያንን አገኘና እነርሱ ከባርነት ነጻ አወጡት፡፡ በ1864 ዓ.ም. ዕለተ ትንሣኤም ጥምቀተ ክርስትናን ተቀብሎ “ኦኔሲሞስ” የሚል የክርስትና ስም ተሰጠው፤ ትርጓሜውም በግሪክኛ “ጠቃሚ” ማለት ነው፡፡
ስዊድናውያኑ ይኽን ልጅ ትምህርት ቤታቸው ውስጥ ትምህርት እንዲከታተል አደረጉት፡፡ ያሳይ የነበረውን የትምህርት ብቃትም ተመልክተው ለበለጠ ትምህርት ወደ ሀገረ ስዊድን ላኩት፡፡ እዚያም በትምህርት ረዘም ላለ ጊዜ ከቆየ በኋላ  በ1874 ወደ ምፅዋ በመመለስ ምሕረት ኃይሉ የተባለች ቆንጆ አግብቶ ምፅዋ ውስጥ ይገኝ በነበረ ትምህርት ቤት ሲያስተምር ቆየ፡፡    

Wednesday, January 8, 2014

ልጇን በሆዷ የቀበረችው እናት

ውብ የአማርኛ ቃል ግጥሞች ከሚነሡባቸውና ከሚያነሡዋቸው ዐበይት ጉዳዮች መካከል የረኀብንና ሞትን ያኽል ሰፊ ቦታ የሚይዝ ሌላ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም፡፡ የዶ/ር ፈቃደ አዘዘን “ሰሚ ያጡ ድምፆች” ወይም “Unheard Voices” የተሰኘ መጽሐፍ ያነበበ ሰው የምለውን ነገር ይረዳኛል፡፡ ላለፉት ብዙ ምዕታተ ዓመት ረኃብና ሞት የታሪካችን ብቻ ሳይኾን የኪነታችን አካል እንደነበሩና ዛሬም እንዳሉ ሲታወሰኝ፣ “ኹሉን ይለውጣል” የሚባልለት ጊዜ እንዴት እኛን ሳይለውጠን (ሳንለወጥለት?) እንደቀረን እንዳስብ እገደዳለኹ፤ ልክ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ቴዎድሮስ የተሰኘው ተውኔቱ ላይ “እኮ ምንድነን?! ምንድነን?!” ብሎ እንደጠየቀው እኔም ልጠይቅ እነሣለኹ፡፡ ምን ዓይነት ከስሕተታችን የማንማር፣ ለችግር መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ ችግርን መልመድ የሚቀልለን ሰዎች ኾነን ይኾን ብዬም እጠይቃለኹ፡፡ ለማንኛውም ብዙ ሳልጨቀጭቃችኹ ዛሬ ወደማካፍላችኹ ነገር ልውሰዳችኹ፡፡ የቀነጨብኹት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ “የልቅሶ ዜማ ግጥም” ብለው የዛሬ ዘጠና አራት ዓመት ገደማ ካሳተሙት መጽሐፍ ላይ ነው፡፡ እንዲኽ ይላል፡-

Wednesday, January 1, 2014

Do you know the European calendar is four months late?




Quite a number of people, both foreigners and Ethiopians, say the Ethiopian calendar lags seven years behind the European calendar. But, what if I tell you, that is a complete misunderstanding? Seriously!

The specialist on the traditional Ethiopian calendar, Henok Yared[1], writes, Ethiopia has three types of calendars, namely the Solar, the Lunar and the Luni-Solar. All the three types of calendars have their own specific usage among the traditional Ethiopian scholars and the Ethiopian church. The lunar is used during liturgical and non-liturgical prayers, while the solar, the most popular one, is the standard one used to mark the years and all the official business of the society. The Luni-Solar one is used to reckon the starting day of Lent (hudadie/ abiy tsom) and the day of Easter festival. According to the Luni-Solar calendar Ethiopia has already started the year 2014 on Meskerem 1 (September 11); hence, we are in the fourth month since the year 2014 started. So, it will be totally wrong, according to Henok, to say the Ethiopian calendar lags eight years behind. 

Wait, I have something more.