በጉርምስናዬ ጊዜ ሐሳቤ ወሰን አልነበረውምና ዓለምን ሁሉ ለመለወጥ አስብ ነበር፡፡ እድሜዬና ብስለቴ እየጨመረ ሲመጣ ዓለምን መለወጥ እንደማይቻል ተገነዘብሁ፡፡ ስለዚህም ግቤን ጠበብ አድርጌ ሀገሬን ብቻ ለመለወጥ ወሰንሁ፡፡
ነገር ግን እርሷም ጨርሶ የምትለወጥ አልሆነችም፡፡
የጉልምስናዬ ወራት ካለፈ በኋላ ቤተሰቤንና በቅርቤ ያሉትን ሰዎች በመለወጥ ላይ አተኮርሁ፡፡ ይሁን እንጂ ይህም ውጤት አልባ ነበረ፡፡
አሁን በሞት ልጠቀለል ጥቂት በቀረኝ ሰዐት በድንገት የሚከተለውን እውነታ ተረዳሁ፡፡
መጀመሪያ ራሴን ለውጬ ቢሆን ኖሮ፣ ቤተሰቤ የእኔን ምሳሌ ተከትሎ በተለወጠልኝ፤ በቤተሰቤ ውስጥ ባገኘሁት ለውጥ አነሳሽነትና አበረታችነትም ሀገሬን ማሻሻል በቻልሁ ነበረ፡፡ ማን ያውቃል?! ይሄኔ ዓለምንም ለውጬ ይሆን ነበር፡፡ ነበረ፡፡ ነበረ፡፡ ነበረ...
No comments:
Post a Comment