በ1881 ዓ.ም. ልክ በዛሬዋ መጋቢት 1 ዕለት
አፄ ዮሐንስ ራስ አርአያን፣ ንጉሥ ሚካኤልን፣ ራስ ኃይለ ማርያምን፣ ራስ አሉላን፣ ራስ መንገሻንና ራስ ሐጎስን ይዘው መተማ ላይ
ከደርቡሽ ጋር ጦርነት ገጠሙ፡፡ ከጅማሮው ላይ ጦርነቱን በኃያልነት እያሸነፉ ቢቆዩም እርሳቸው ድንገት ተመትተው፣ ጦሩም ድንገት
ተፍረክርኮ ሽንፈት አይቀሬ ኾነ፡፡ መጋቢት 2 ቀንም ደርቡሽም የንጉሡን ጭንቅላታቸውን ቆርጦ ወሰደ፡፡ አልቃሽም ቀጥሎ ያለውን ሙሾ
ደረደረችላቸው ይባላል፡፡
አፄ ዮሐንስ ይዋሻሉ፣
“መጠጥ አልጠጣም” እያሉ፣
ሲጠጡም አይተናል በርግጥ፣
ራስ የሚያዞር መጠጥ፡፡
በጎንደር በመተኮስ፣
በደምቢያ መታረድ አዝኖ ዮሐንስ፣
ደሙን አፈሰሰ እንደ ክርስቶስ፡፡
እንዳያምረው ብሎ ድኃ ወዳጁን፣
መተማ አፈሰሰው ዮሐንስ ጠጁን፡፡
የጎንደር ሃይማኖት ቆማ ስታለቅስ፣
አንገቱን ሰጠላት ዳግማይ ዮሐንስ፡፡
(ምንጭ፡- ቦጋለ ተፈሪ በዙ፡፡ ትንቢተ ሸሕ ሑሴን ጅብሪል፡፡ ዐዲስ ዐበባ፣ እታፍዘር አታሚዎች፣ 1994)
No comments:
Post a Comment