Thursday, February 21, 2013

“ከቶ አታጥበኝም!”



ታጥቀኽ ጨርቅን ለማበሻ፣
ልታጥበኝ እግሬን ስትሻ፣
“ከቶ አታጥበኝም!” ብዬ፣
በግብዝነት ተሰናክዬ፣
መስቀሌን ከእኔ እንዳላርቅ፣
   በ“እኔ” ታንቃ ነፍሴ እንዳትማቅቅ::


የጌቴሴማኒን ሐዘን ጭንቀት፣ የጲላጦስን አለንጋ፣
የጭፍሮችን የሾኽ አክሊል፣ የሄሮድስን ቀይ ካባ፣
የመስቀልን ጽዋ ተርታ፣
የጎልጎታን ዕድል ፈንታ፣
ፈርታ…
ሳትካፈል እንዳትቀር የትንሣኤኽን ሰላምታ…

አሜን! ውዴ ሆይ! እጠበኝ፡፡





ገመዴ ባማረው ስፍራ፣ በአንተነትኽ ላይ ትውደቅ፤
ርስቴም መስቀልኽ ኾኖ ዘለዓለም ፏ! ብሎ ይድመቅ፤
ነፍሴ ካለማመኗ፣ ከፍርኀቷ ዕድፍ ትላቀቅ፡፡

አሜን፡፡ አባቴ፡፡
በሂሶጵ እርጨኝ እጠበኝና፣
ዕድሌ በዕድልኽ ይጽና፡፡
                                 

2 comments:

  1. It reminds me of this verse "ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ::"
    አብዝተህ ጻፍ ወዳጄ ሆይ!

    ReplyDelete
  2. Tebarek Mehariye! Amen!

    ReplyDelete