በዚህ ዓለም ስትኖር በልብኽ
ውስጥ ያስቀመጥኹት የእኔነቴ ኮከብ አለ፡፡ ይህን ኮከብ ከሑከትና ሩጫ ጨለማ ዘወር ብለኽ፣ በፀጥታና በጸሎት ብርሃን ስትፈልገው
ታገኘዋለኽ፡፡ የህልውናኽ አልፋና ዖሜጋ፣ የሕይወትኽ ትርጉም ወደ ኾንኹት ወደ እኔ፣ ወደ አባትኽ ይመራኻልና ተከተለው፡፡ ኮከቡን
የመከተል ጉዞኽን ስትጀምር የዚህ ዓለም ገዢ “ማነኽ ወዴት ነኽ? ማን ስለኾንኽ ነው ይህን ጉዞ የጀመርኸው?” የሚሉ ጥያቄዎችን
ያቀርብልኻል፡፡
መልስኽ እንዲህ ይኹን፡-
“እኔ ዩኒቨርሱን በእጆቹ ያበጃጀው የፍቅር ባርያ ነኝ፡፡ እርሱ በልቡናዬ ያስቀመጠልኝን ኮከብ ተከትዬ እየኼድኹ ነው፡፡ ዓላማዬም
ለንጉሤ እኔነቴን እጅ መንሻ ማቅረብ ነው፡፡ ጉዞው ረጅም፣ መንገዱም ውጣ ውረድ የበዛበት እንደኾነ፣ ከእኔ የተሻለ ዐቅም ያላቸውን
እንኳን አዳክሞ መግደል የቻለ ከባድ መንገድ እንደኾነ ዐውቃለኹ፤ ግን የጠራኝ እርሱ ኃይሌ ስለኾነልኝ ጉዞዬን እንደምፈጽመው አምናለኹ፡፡
ስሙ መጠጊያዬ፣ ኃይሉ ድጋፌ፣ ፍቅሩ መጽናኛዬ፣ ብርታቱም ምርኩዜ ናቸው፡፡”
ገዢው ሊያታልልኽ “ተመልሰኽ
ና!” ይልኻል፡፡ አንተ ግን በአዲሱ መንገድኽ ኺድ፡፡ ዕለት ዕለት ኮከብኽን ተከተል፡፡ ዕለት ዕለት ንጉሥኽን አግኘው፡፡ ዕለት
ዕለት አንተነትኽን ለንግሥናው፣ ለማይነገረው ታላቅና ጥልቅ ፍቅሩ አቅርብለት፡፡ በእውነት ይገባዋልና!
Amen!
ReplyDeleteእንዴት የተዋበ ምክር ነው?! እጆችህ ይባርኩ ደግመህ ደጋግመህ ጻፍ::
Amen.
ReplyDelete